Friday, February 21, 2014

ምሥጢረ ጥምቀት ክፍል-3

ሠ-በማን ስም ልንጠመቅ ይገባል

  ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰዎች የእግዚአብሔርን ልጆች ይሆኑ ዘንድ በሥላሴ ስም ታጠምቃለች፡፡ ይህም ጌታ ራሱ ለሐዋርያቱ ‹‹ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም  ያጠመቃችኋቸው፡፡››  (ማቴ. 28÷19) ብሎ የሰጠውን አምላካዊ ቃል መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ደም ከተመሠረተችበት ዘመን አንስቶ በሥላሴ (በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ) ስም መጠመቅ የድኀነት በር ቁልፍ መሆኑን ስታስተምርና ተግባራዊ ስታደርግም ኖራለች፡፡

ምሥጢረ ጥምቀት- ክፍል-2

ሐ-የጥምቀት ምሳሌ በብሉይ ኪዳን

ኖኀና ቤተሰቡ ከጥፋት የዳኑባት መርከብ የአማናዊቱ ቤተክርስቲያን ምሳሌ መሆንዋ በመጽሐፍ ቅዱስ የተረጋገጠ ነው፡፡ ፈሪሃ እግዚአብሔር በልቡናቸው ያደረው ኖኀና ቤተሰቡ ከጥፋት ሲድኑ እግዚአብሔርን ድምፅ ያልሰሙት የኖኀ ዘመን ለአማናዊው ጥምቀት ምሳሌነት እንዳለው ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ሲገልጽ (ሲያስተምር) #ጥቂቶች ማለትም ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኀ ዘመን በቆየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም፡፡
ፈሪሃ እግዚአብሔር በልቡናቸው ያደረው ኖኀና ቤተሰቡ ከጥፋት ሲድኑ እግዚአብሔርን ድምፅ ያልሰሙት የኖኀ ዘመን ለአማናዊው ጥምቀት ምሳሌነት እንዳለው ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ሲገልጽ (ሲያስተምር) ‹‹ጥቂቶች ማለትም ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኀ ዘመን በቆየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም፡፡ ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድናል፡፡ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ›› 1ጴጥ.3÷20-12፡፡

ምሥጢረ ጥምቀት

ክፍል-1
ሀ-አስፈላጊነት


መጠመቅ ማለት መነከር፣ መዘፈቅ፣ ውኃ ውስጥ ገብቶ መውጣት ማለት ነው፡፡ ምሥጢረ ጥምቀት የሥላሴ ልጅነት የሚሰጥበት እና የኃጢአት ሥርየት የሚገኝበት ምሥጢር ነው፡፡
1.      ድኀነትበጥምቀትነው፤
ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን ያልተጠመቀ ሰው አይድንም፡፡ የተጠመቀ ግን እንደሚድን በመዋዕለ ትምህርቱ እዲህ ሲል አስተምራል #ያመነ የተጠመቀም ይድናል$ ማር.16 ቁ 16፡፡ ያመነ ይድናል ብቻ አለማለቱን ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ ጥምቀት ለድኀነት ባያስፈልግ ኖሮ ጌታ ያመነ የተጠመቀም ይድናል ባላለ ነበር፡፡

Monday, September 9, 2013

እንግዲህስ ለንሰሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የማኅበረ በዓለወልድ ሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከት ፱ኛ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ በመልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው "እንግዲህስ ለንሰሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ" በሚል የተላለፈው ትምህርት በካልጋሪ ካናዳ ሐምሌ ፳፻፭ ዓ.ም. ምዕመናን ይማሩበት እና ይጠቀሙበት ዘንድ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።
ለመምህራችን መልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው ቃለ ሕይወትን ያሰማልን።
ማኅበረ በዓለ ወልድ ሰሜን አሜሪካ

Saturday, July 27, 2013

እንኳን ለ፱ኛው ዓመታዊ ጉባኤ በሰላም አደረሰን


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አምላክ፥ አሜን። 
“የአምላካችንን ቤት ከቶ አንተውም።” ነህምያ ፲፥፴፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርቲያን በረ በዓለ ወልድ በሰሜን አሜሪካ ፱ኛ ዓመታዊ ጉባዔ እነሆ ለመጀመሪያ ጊዜ በካናዳ ምድር ካልጋሪ ከተማ ከመላው የአሜሪካ እና የካናዳ ከተሞች በመጡ የማኅበሩ አባላት በድምቀት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
መላው የማኅበሩ አባላትና የማኅበረ በዓለ ወልድ ወዳጆች እንኳን በሰላምና በጤና ለዚህ ቀን አደረሳችሁ። እግዚአብሔር ጉባዔውን የበረከት ያደርግልን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።አሜን።

Thursday, July 18, 2013

፱ኛው ዓመታዊው የማኅበረ በዓለ ወልድ ጉባኤ ደረሰ በካልካሪ ካናዳ ዝግጅቱ ተጠናቋል


የሚሰማምይበልየተጠማም  ይምጣ የወደደም የሕይወትን ውኃ
እንዲያው ይውሰድ“ ራዕየ ዮሐንስ ፳፪፥፲፯

በሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከት የማኅበረ በዓለ ወልድ ፱ኛ ዓመት መንፈሳዊ ጉባኤ በካልጋሪ ካናዳ ዝግጅቱን አጠናቆ ከመላው አሜሪካ እና ካናዳ የሚመጡትን ካህናት አባቶች፣ ዲያቆናት፣ ሰባኬያነ ወንጌል፣ ዘማሪያን እንዲሁም ምዕመናን እና ምዕመናት በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። በዚህ ጉባኤ ላይ ከመላው አሜሪካ እና ካናዳ የሚመጡ ተጋባዥ እንግዶች እና ከተለያዩ ከተሞች በሚመጡ የማኅበሩ አባላት ለሦስት ቀናት የተዘጋጀውን ዝግጅት ለመቋደስ ነፍሳችንን በቃለ እግዚአብሔር ለማሳነጽ ብሎም በዝማሬ እግዚአብሔርን ለማገልገል በዝግጅት ላይ እንገኛለን። እርሶስ? ዝግጅትዎን አጠናቀዋል? የቀሩት ቀናት ጥቂት ቢሆኑም ለዝግጅት ግን በቂ እንደሚሆን እናምናልን። 
ከዚህ በተጨማሪ የማኅበረ በዓለ ወልድ ካናዳ ቀጠና ላለፉት ስድስት ወራት በተከታታይ በመገናኘት ዝግጅቱን ያማረ ለማድረግ እና እግዚአብሔር የሚከብርበት ጉባኤ ለማካሄድ ደፋ ቀና ሲሉ ቆይተዋል በመሆኑም በመላው ዓለም የምንገኝ ምዕመናን በዚሁ በዓል በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን የካናዳው ማኅበረ በዓለ ወልድ በታላቅ አክብሮት ይጋብዛል።
አስታውሱ: ሐምሌ ፳፩ እና ፳፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. (July 27 & 28, 2013)
               በሐመረ ኖሕ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን 
       618 – 2nd Ave NE. Calgary, Canada 
ለተጨማሪ መረጃዎች በሚከተሉት ቁጥሮች ይደውሉ
403-402-7585 / 403-542-7980 / 403-975-0141
ማኅበረ በዓለ ወልድ ካናዳ

Monday, April 1, 2013

ማኅበረ በዓለወልድ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር የአርባምንጭ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም የአብነት ት/ቤት ግንባታ ሊያስገነባ ነው

የመሰረት ድንጋዩ በተጣለበት ቦታ

በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ 
መጋቢት ፲፭ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የማኅበረ በዓለወልድ ሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከት ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር በጋሞጎፋ ሃገረ ስብከት በአርባ ምንጭ ደብረጽዮን ቅድስት ማርያም ገዳም ያአብነት ትምሕርት ቤት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ በሃገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ አማካኝነት የመሠረት ድንጋዩ ተጥሏል።

የፕሮጀክቱ ስም:
ለጋሙጎፋ ሀገረ ስብከት በአርባ ምንጭ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ገዳም የአብነት ትምሕርት ቤት
ግንባታ።

Wednesday, February 6, 2013

የብሕትውና(የምንኩስና) ኑሮ - ክፍል 3


ምንኵስና በኢትዮጵያ
4ኛው // በፊት
ሥርዓተ ምንኵስና ወደ ሀገራችን የገባው በኢትዮጵያ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ በአባ ጳኩሚስ ዘመን ቢሆንም የብሕትውና ኑሮ ግን በሀገራችን ከዚያም ቀድሞ እንደነበረ የሚጠቁሙ አንዳንድ መረጃዎች አሉ፡፡
አባ አሞንዮስ፡- ሥርዓተ ምንኵስና ወደ ኢትዮጵያ ከመግባቱ በፊት አሞንዮስ የተባሉ ባሕታዊ በተንቤን ቆላ ደብረ አንሣ በተባለው በረሃ በጾም በጸሎት ተወስነው ይኖሩ ነበር፡፡

አባ ዮሐኒ፡- በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መግቢያ ላይ በትግራይ ተንቤን አውራጃ በሀገረ ሰላም ቀበሌ ተወለዱ፡፡ በዚያን ዘመን ሥርዓተ ምንኵስና ወደ ኢትዮጵያ ባይገባም አበው በምናኔ በበረሃ ይኖሩ ነበር፡፡ የአባ ዮሐኒ ቤተሰቦች ድሆች ስለነበሩ አባ አሞንዮስ ወስደው አሳደጓቸው፡፡ ካደጉ በኋላም ከአባ አሞንዮስ ተለይተው ወደ በረሃ ለብቻቸው በመውረድ በተጋድሎ ሲኖሩ ከቆዩ በኋላ በተወለዱ 3 ዓመታቸው ኀዳር 5 ቀን እግዚአብሔር ወደ ብሔረ ሕያዋን በመላእክት እጅ እንደወሰዳቸው ገድለ አባ ዮሐኒ ይገልጣል፡፡

የብሕትውና(የምንኩስና) ኑሮ - ክፍል 2



2. የሥርዓተ ምንኩስና ታሪክ

 2.1   - አባ ጳውሊ  እና  አባ እንጦንስ

    2.1.1-  አባ ጳውሊ

አባ ጳውሊ  እና  አባ እንጦንስ
አባ ጳውሊ  እና  አባ እንጦንስ
በተባሕትዎ መኖር ከጥንት ዘመን የመጣ ይሁን እንጂ የብሕትውናን ኑሮ ሥርዓት በወጣለት መልኩ የጀመረው አባ ጳውሊ የተባለው ግብፃዊ አባት ነው፡፡ በንጉሥ ዳክዮስ ዘመነ መንግሥት በክርስቲያኖች ላይ በተነሣው ስደት ምክንያት አባ ጳውሊና ቆይቶም ደግሞ ሌሎች የአካባቢው ክርስቲያኖች በግብፅ በረሃዎች ውስጥ በምናኔ ይኖሩ ነበር፡፡
ይህንን አባ ጳውሊ የጀመረውን ሥርዓት አጠናክሮ ለማስፋፋት ያበቃው ደግሞ አባታችን አባ እንጦንስ ነው (251-356..)፡፡

  2.1.2- አባ እንጦንስ
አባ እንጦንስ ግብፅ ውስጥ ቆማ በተባለች መንደር ከሀብታም ቤተሰቦች 251 . ተወለደ፡፡ ወዳጆቹ ገና 2 ዓመት ወጣት እያለ ስላረፉ በማቴ.19÷21 ላይ ያለውን ትምህርት መሠረት አድርጐ የወረሰውን ሀብት በሙሉ በመሸጥ ለድኾች አከፋፈለና ወደ ግብፅ በረሃ በመውረድ 85 ዓመት በተጋድሎ ኖሯል፡፡

የብሕትውና(የምንኩስና) ኑሮ - ክፍል 1


1.አጀማመር
1.1 በሕገ ልቡና

የብሕትውና ኑሮ የተጀመረው ከሰው ልጅ ወደዚህች ምድር መምጣት አንሥቶ ነው፡፡ ደቂቀ ሴት ከቃየል ልጆች ኑሮና ግብር ተለይተው በደብር ቅዱስ በንጽሕና በቅድስና ይኖሩ እንደነበር ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል( ዘፍ.6÷1-3 ሄኖክ 2÷1-2)
አባታችን ሄኖክም በዘመኑ ከነበሩት ግብረ ሰዶማውያን ርቆ፣ ሰዎችን ለጥፋት ውኃ ከዳረገው ኃጢአት ተለይቶ፣ ንጹሕ እግዚአብሔር ንጽሕናን ይሻል በማለት በሕገ ልቡና ተመርቶ በእግረ ገነት ለሰባት ዓመታት በብሕትውና ከኖረ በኋላ በልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ ከአካለ ሥጋ ወደ ብሔረ ሕያዋን መነጠቁን መጽሐፈ ሄኖክ ያስረዳል፡፡ የመልከ ጼዴቅም የኑሮ ሥርዓት ይህንኑ የባሕታውያን ሕይወት የተከተለ ነበር( ዘፍ.14÷17-24)፡፡

Tuesday, January 22, 2013

የመገለጥ ሃይማኖት በአስተርእዮ


በዲያቆን ብርሃኑ አድማስ
የጥምቀት በዓል አከባበር በጎንደር ከተማ
ሃይማኖት የምንቀበለውና የምንጠብቀው እንጂ የምንሠራውና የምናሻሽለው አይደለም ከታኅሣሥ 29 ቀን ጀምሮ እስከ ዐቢይ ጾም መግቢያ ድረስ ያለው ወቅት /ጊዜ/ ዘመነ አስተርእዮ /የመገለጥ ወራት/ እየተባለ ይጠራል፡፡ በታኅሣሥ 29 ቀን የጌታችን ልደት ስለሆነ በዚህ አምላክ በሥጋ የተገለጠበት በዓል ይከበራል፡፡ ጥር 11 ቀን ደግሞ በጌታችን ጥምቀት የሥላሴ አንድነት ሦስትነት በይፋ የተገለጠበት ነው፡፡ ጥር 12 ቀን ደግሞ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ማስተማር በጀመረበት ጊዜ በቃና ዘገሊላ ሰርግ ቤት ተገኝቶ ውኃውን ወደ ወይን በመለወጥ አምላክነቱን በይፋ የገለጠበት በዓል ነው፡፡ እነዚህ ሦስት ዓበይት መገለጦች ወቅቱን በአጠቃላይ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የተገለጠበትን መታሰቢያ አደረጉት፡፡ አምልኮተ እግዚአብሔርን ትክክለኛ ሃይማኖት ከሚያሰኙት መሠረታዊ ነጥቦች ዋነኛውና ቀዳሚው የመገለጥ ሃይማኖት /Revealed Religion/ መሆኑ ነው፡፡